InternationalNews

የአሜሪካ ተቀባይነት ማሽቆልቆል

አሜሪካ በዓለምአቀፍ ደረጃ የነበራት ተቀባይነት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ማሽቆልቀሉ እንዲሁም ከሩሲያና እስራኤል ቀጥሎ የዓለም ስጋት ተደርጋ መቆጠር መጀመሯን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

አንድ የዴንማርክ የዴሞክራሲ ተቋም በ98 የዓለም ሀገራት የሚገኙ ከ94 ሺህ በላይ ሰዎችን በናሙናነት ወስጄ አከናወንኩት ባለው ዓለምአቀፍ ጥናት ፕሬዝዳንት ትራምፕ እየተከተሉት ያለው ፖሊሲ የአሜሪካን ዓለምአቀፍ ተቀባይነት እየሸረሸረው መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር በዓለም ሀገራት ላይ የጣለው ታሪፍ እንዲሁም ከአውሮፓ ሀገራትና ካናዳ ጋር የገባበት ውዝግብ ለአሜሪካ ተቀባይነትና ተሰሚነት ደረጃ መውረድ በጥናቱ እንደምክንያት የተቀመጡ ነጥቦች መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews