EthiopiaNews

የአየር መንገዱ ግዥ

🔸የኢዮጵያ አየር መንገድ 25 አነስተኛ አውሮፕላኖች አዲስ የግዥ ትእዛዝን በተመለከተ በሚቀጥሉት 3 ወራት ውስጥ ውሳኔ ሊሰጥ እንደሚችል ተነገረ።

🔸የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው የ25 አነስተኛ አውሮፕላኖች ትእዛዝ አስመልክቶ ያልተፈቱ አንዳንድ ጉዳዮች እንዳሉ ጠቅሰው በ3 ወራት ውስጥ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል ብለዋል።

🔸ዋና ስራ አስፈፃሚው አየር መንገዱ ሊገዛ ያሰባቸው 25ቱ አነስተኛ አውሮፕላኖች የሀገር ውስጥ እና የጎረቤት ሀገራት በረራን ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል።

🔸ዋና ስራ አስፈፃሚው አየር መንገዱ አሁን ላይ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንደሌለበት ለሮይተርስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews