EthiopiaLatestNews

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት ታሪፍ..

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያው ተጠናቆ ይፋ እስከሚደረግ ጊዜ ድረስ ቀደም ሲል የነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎት እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ተከትሎ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል ያስታወቀው የትራንስፖርት ቢሮው በአገልግሎቱ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናት አድርጎ በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነና በቀጣይ ቀናት ይፋ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም አመልክቷል፡፡በመሆኑም በከተማዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎች የታሪፍ መጠኑ ይፋ ሳይሆን ምንም ዓይነት ዋጋ ሳይጨምሩ አገልግሎቱን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል። መረጃውን ከትራንስፖርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ነው፡፡ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።Telegram: https://t.me/ebstvworldwideFollow us on: https://linktr.ee/ebstelevision#ኢቢኤስ#EBS