የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ76ኛ ዙር ያስተማራቸውን 6 ሺህ 417 ተማሪዎችን አስመረቀ።
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትር እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ፍሬህይወት ታምሩ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡
ዛሬ የተመረቁት ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ እና የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የዛሬ ተመራቂዎች በአዲሱ የትምህርት ሪፎርም የተመረቁ የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ተመራቂዎች በሚሰማሩበት የስራ ዘርፍ በሀገር ፍቅርና በታማኝነት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
