EthiopiaNews

የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን

የአፍሪካ ህብረት የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 ቀን  2018 አ.ም የሚደረገውን  የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚታዘብ  ታዛቢ ቡድን መላኩን አስታወቀ።

ህብረቱ ባወጣው መግለጫ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራው የታዛቢ ቡድን አዲስ አበባ መግባቱን ገልጿል።

ታዛቢ ቡድኑ ከ37 ሀገራት የተውጣጡ አምባሳደሮች ፣ የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ባለሙያዎች ፣ የሚዲያ አካላት ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ የሲቪክ ማህበራት ያካተተ መሆኑን ህብረቱ ገልጿል።

የምርጫ ታዛቢ ቡድኑ 73 አባላት ያሉት ሲሆን 61 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው ተብሏል።

ቡድኑ ምርጫውን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ግንቦት 26 2018 አ.ም በአዲስ አበባ በሚያካሂደው  ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፆ የመጨረሻ የተጠቃለለ ሪፖርቱን ደግሞ ከ2 ወራት በኋላ በይፋ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። መረጃው ከአፍሪካ ህብረት የተገኘ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews