BusinessEthiopiaNews

የአፍሪካ ልማት ባንክ ኮሮናን ለመከላከል 27.33 ሚሊየን ዶላር አጸደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ በአህጉሪቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ለሚደረገው እንቅስቃሴ 27.33 ሚሊየን ዶላር ማጽደቁን አስታውቋል፡፡

ይህ የፋይናንስ ድጋፍ በኮቪድ 19 ላይ የተቀናጀ አፍሪካዊ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ አቅም እንደሚሰጥ ነው የተገለጸው፡፡

በዋናነትም በወረርሽኙ ምክንያት የደረሰውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽህኖ ለመቋቋም ያግዛልም ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም ድጋፉ የአፍሪካን የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላትን በመደገፍ በአፍሪካ ልማት ፈንድ በኩል ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው አገራት ቴክኒካዊ እገዛ እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡

በልማት ባንኩ የሚደረጉ ድጋፎች በአፍሪካ አገራት የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል በአየር በባህርና በመሬትና ለሚከናወነው ተግባራት ያለግላሉ መባሉን ኒው ታይምስን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡