EthiopiaLatestNews

የኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሰላም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ ለመስራት የትብብር ስምምነት ተፈራረመ።

የኢቢ ኤስ ቴሌቪዥን በሰላም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ ለመስራት የትብብር ስምምነት ተፈራረመ። ሁለቱ ተቋማት በትብብር ለመስራት የተሰማሙት በተለይም አዲሱ ትውልድ ሃይማኖት፣ ብሔርና ቋንቋ ሳይለያየው በሰላም ጉዳይ ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማስቻል ነው ተብሏል። ጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቭዥን ድርጅትም ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዘጋጅነት የተካሄዱ የምህላ ጸሎት መርሃ ግብሮችን በነጻ በማስተላለፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ገልጿል።