EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 277.49 ቢሊዮን ብር ግብር እና ቀረጥ መክፈሉን አስታወቀ።

ይህ የተነገረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የ10 ወራት የእቅድ አፈፃፀም በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ 101,862 አዳዲስ የስራ ዕድሎችን በመፍጠር የዕቅዱን 124 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።መረጃው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv