የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2019 በጀት ዓመት የ10 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 25ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የፌዴራል መንግስት የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት መግለጫን ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ በተያዘው በጀት ዓመት ከመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የመነጩ ጫናዎችን በመቋቋም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ10 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት እንደሚመዘገብ መገመቱን ጠቅሰዋል፡፡
ከ2012 እስከ 2016 ባሉት ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአማካይ በየዓመቱ የ6 ነጥብ 8 በመቶ እንዲሁም በ2017 የ9 ነጥብ 2 በመቶ እድገት መመዝገቡን ያነሱት ሚኒስትሩ በቀጣዩ በጀት አመት ደግሞ የ10 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ይመዘገባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ጨምረውም በ2018 በጀት ዓመት 10 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።
የውጭ ንግዱ ገቢ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ38 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ማሳየቱን ጠቅሰው፤ የበጀት አመቱ ሲጠናቀቅ 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ መገመቱን ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የበጀት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
