የኢትዮጵያ እና የአይ ኤም ኤፍ ውይይት
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከአለም አቀፉ የገንዘብ ደርጅት ጋር በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ እና በኢኮኖሚ ማሻሻያው ላይ መወያየቱ ተነገረ።
በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኒጄል ክላርክ ጋር ገንቢ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱ ያተኮረው በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አተያይ፣ የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳው ቀጣይነት ባለው ትግበራ እና እየተለወጠ ባለው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አካባቢ አንድምታ ላይ ነበር ተብሏል።
በውይይቱ ወቅት፣ ልዑካኑ ስለ ኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም እና እይታ ወቅታዊ መረጃ አቅርበው፣ የሪፎርም ፕሮግራሙን በማራመድ ረገድ ጠንካራ ተቋማዊ ቅንጅት መታየቱን አስረድተዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ የሪፎርም ስራዎቹ ለችግሮች ምላሽ ሰጪ፣ ዘላቂ እና ከኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የልማት ግቦች ጋር በጥብቅ የተጣጣሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአለም የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የማሻሻያ ፕሮግራሙ ጠንካራ አፈጻጸም እያሳየ መሆኑን ገልፆ የማሻሻያውን ፍጥነት መጠበቅ እና የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ይበልጥ ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብሏል።
መረጃው የተገኘው በአሜሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
