የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና የአዲስ አበባ ሀገረሰብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ በገዛ ፈቃዳቸው ሐዋርያዊ ኃላፊነታቸውን ማስረከባቸው ተገለጸ።
ቫቲካን ለሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቅድስት መንበር ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በዛሬው ዕለት ጥያቄያቸውን መቀበላቸው ነው የተገለጸው፡፡
የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ተተኪ በመሆን የአዲስ አበባ ረዳት ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው መሾማቸውንም የቤተክርስቲያኗ መረጃ ያመለክታል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
