Sports

የኢትዮጵያ የአለም ሻምፒዮና ተሳትፎና ድል

በአለም ሻምፒዮና ታሪክ የደመቀ ውጤት ካላቸው ሀገራት ተርታ የምትመደበው ኢትዮጵያ በሄልሲንኪ በተደረገው የመጀመሪያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጀምሮ እስካሁን በተካሄዱት ውድድሮች በሙሉም ተሳትፎዋን አድርጋለች፡፡

በመጀመሪያ ተሳትፎዋ በአትሌት ከበደ ባልቻ የማራቶን የብር ሜዳሊያ አሃዱ ብላ የሜዳሊያ ስኬቷን የጀመረችው ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር 1987 በሮም ከተደረገው የአለም ሻምፒዮና በቀር በሁሉም የአለም ሻምፒዮናዎች ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች፡፡

በተለይም ኢትዮጵያ በረዥም ርቀት ስመ ጥር የሆኑ አትሌቶችን በየጊዜው በማፍራት በአለም ሻምፒዮናው በርቀቱ በርካታ ሜዳሊያዎችን ማስመዝገቧም አይዘነጋም፡፡

ገና በለጋ እድሜዋ ከተሳተፈችበት የፓሪስ አለም ሻምፒዮና ጀምሮ እስከ 2017ቱ የለንደን አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5 ወርቅ፣ሁለት ብርና 1 የነሃስ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ስሟን በደማቅ ያጻፈችው ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶች ለኢትዮጵያ በርካታ ሜዳሊያዎችን ማስመዝገብ ከቻሉ አትሌቶች በቀዳሚነት ትቀመጣለች፡

እንደ ጥሩነሽ ሁሉ በአለም ሻምፒዮና የእትዮጵያን ሰንደቅ ደጋግሞ ከፍ ያደረገው ቀነኒሳ በቀለ 5 የወርቅ እና 1 የነሃስ ሜዳሊያን ማስመዝገብ የቻለ ስመ ጥር አትሌት ነው፡፡
ከነዚህ በተጨማሪ እንደነ ሃይሌ ገብረስላሴ፣ደራርቱ ቱሉ መሰረት ደፋር አልማዝ አያና እና ሌሊሳ ዴሲሳ ያሉ አትሌቶችም ለኢትዮጵያ በርካታ ሜዳሊያዎችን ካስገኙ አትሌቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ኢትዮጵያ እስካሁን በተደረጉ 18 የአለም ሻምፒዮና ውድድሮች 33 የወርቅ፣34 የብርና 28 የነሃስ በአጠቃላይ 95 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአለም 6ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከተገኙት ሜዳሊያዎች መካከል አብዛኞቹ የተገኙት በረዥም ርቀት ነው፡፡ሪፖርተ፡ ሳምራዊት ሐብቴ

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS