EthiopiaNews

የኢንሹራንስ ረቂቅ አዋጅ

ብሔራዊ ባንክ አዲስ የኢንሹራንስ ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ።

ባንኩ ይፋ ያደረገው የኢንሹራንስ ረቂቅ አዋጅ የውጭ ኩባንያዎች በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ ድርሻ እንዲይዙ እና ለኢንሹራንስ ድርጅቶች ገለልተኛ ተቆጣጣሪ ተቋም እንዲቋቋም የሚፈቅድ ነው ተብሏል።

ረቂቅ አዋጁ የውጭ ኩባንያዎች በአገር ውስጥ የኢንሹራንስ ድርጅቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ባለቤት የሚሆኑባቸውን ተቀጽላዎች ወይም (ሰብሲዳሪዎች) እንዲያቋቁሙ፣ አክሲዮን እንዲገዙ ወይም የውክልና ቢሮ እንዲከፍቱ ይፈቅዳል።

አንድ የውጭ ስትራቴጂክ ባለሃብት ባንድ የኢንሹራንስ ድርጅት ውስጥ መግዛት የሚችለው አክሲዮን ከ40 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት ረቂቁ የደነገገ ሲሆን፣ ስትራቴጂካዊ ያልሆነ ግለሰብ ባለሃብት ደግሞ መግዛት የሚችለው አክሲዮን ከ7 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት በረቂቅ አዋጁ ተደንግጓል።

መረጃው ከብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv