EthiopiaNews

የእንግሊዝ ኤምባሲ ስለምርጫው

👉የእንግሊዝ ኤምባሲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሳካ ሁኔታ የ7 ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን ማጠናቀቅ መቻሉን አድንቋል።

👉ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።

👉ኤምባሲው በምርጫው የተሳተፉ የምርጫ ተወዳዳሪዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ታዛቢዎች ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ፣ እና ለሌሎችም ያለውን አድናቆት ገልጿል።

👉ኤምባሲው ምርጫውን እየታዘቡት ያሉት የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢዎች ስለምርጫው የሚያወጡትን ሪፖርት እንደሚጠብቅ ነው ያሳወቀው።

👉የአፍሪካ ህብረት እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች ምርጫውን አስመልክቶ ዛሬ ግንቦት 26 2018 አ.ም የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርታቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ከዚህ ቀደም መግለፃቸው ይታወሳል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv