EthiopiaNews

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችላቸውን መስፈርት የያዘ መመሪያ ወጣ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአራት መመዘኛዎች ከ60 ከመቶ በላይ ውጤት ካመጡ ወደ ራስ ገዝነት ሽግግር እንዲያደርጉ የሚያዝ መመሪያ አውጥቷል።

እነዚህ መመዘናዎች ትምህርት ተቋማቱ በአስተዳዳር፣ በፋይናንስ፣ በሰው ኃይል አደረጃጀትና በአካዳሚክ አምዶች ሲሆኑ በተዘጋጀው መመዘኛ መሰረት ዩኒቨርሲዎቹ ከ60 በመቶ በላይ ውጤት ካመጡ ወደ ራስ ገዝነት ሽግግር እንዲጀምሩ መመሪያው ይፈቅዳል።

በዚህም መሰረት በሚደረገው ምዘና  የአስተዳደር አምድ 30 ከመቶ፣ ፋይናንስ 20 ከመቶ፣ ሰው ሃይል 15 እና አካዳሚክ አምድ 35 ከመቶ እንደሚያዝላቸውም በመመሪያው ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡

በተለይ በፋይናንስ መመዘኛ መስፈርት ለሦስት ተከታታይ የቅርብ ዓመታት ኦዲት ያስደረገ እና የኦዲት አፈጻጸም ግምገማ ውጤቱ ንጽህ እና ከተወሰነ በስተቅር ችግር የሌለበት ከሆነ፣ባለፉት ሦስት ተከታታይ አመታት ከጠቅላላ በጀቱ 15 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ሀብት ያመነጨ ከሆነ፣ ተቋሙ ራስ ገዝ እንዲሆን ይፈቅዳል፡፡

በሰው ሃይል ረገድም ሁለተኛ ዲግሪ 60 ከመቶ፣ ሶስተኛ ዲግሪ 40 ከመቶ ያደረሰ ከሆነ፤የተቋሙ አካዳሚክ የሰው ሃይል የአካዳሚክ ማዕረግ ስብጥር ደግሞ ሌክቸረር 46 ከመቶ፣ ረዳት ፕሮፌሰር 31 ከመቶ ፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር 20 ከመቶ፣ ፕሮፈሰርና ከዚያ በላይ 3 ከመቶ መሆን አለበት እንዳለበት መመሪው ያስረዳል።

በተቋም ደረጃም ከተልዕኳቸውና ከትኩረት መስካቸው አንፃር 5 እና ከዛ በላይ የአእምሯዊ ንብረት መብት ያገኘ ፣ዩኒቨርሲቲው 70 ከመቶ እና ከዚያ በላይ የቤተ መፃሀፍት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ያደረገ መሆን እንዳለበትም ተጠቁሟል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv