LatestNews

የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን እየታሰበ ይገኛል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተገኝተዋል።

በበአሉ የዛሬ 84 አመት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም 30 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በግፍ የተጨፈጨፉበት ታሪክ ይታሰባል፡፡

በዕለቱ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በጦር አዛዡ ሩዶልፎ ግራዚያኒ ላይ ቦንብ ወርውረው ጉዳት በማድረሳቸው የጣሊያን ጦር በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ ፈፅሟል፡፡

የሰማዕታቱ ቀን በየዓመቱ የካቲት 12 ቀን የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ አባት አርበኞች እና የተለያየዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታቱ መታሰቢያ ሐውልት ዙሪያ ታስቦ ይውላል፡፡