InternationalLatestNews

ኢጋድ በሞቃዲሾ እየታየ ያለው ያለመረጋጋት እንዳሳሰበው ገለፀ

 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በሞቃዲሾ እየታየ ያለው ያለመረጋጋት እንደሚያሳስበው ገለፀ፡፡ ኢጋድ በሶማሊያ የፖለቲካ መረጋጋት እንዳይፈጠር የሚደረገው ወከባ ተገቢነት የሌለው ነው ሲል ኮንኗል፡፡ እየታየ ያለው ያለመረጋጋት ሀገሪቷን ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ላይ ጥላ ሊያጠላ እንደሚችልም አሳስቧል፡፡ በሀገር ግንባታ፣ ሀገሪቷ በምታካሂደው ምርጫ እና ሽብርተኞችን መዋጋት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ነው ኢጋድ የገለፀው፡፡ ፖለቲከኞችም ነገሮችን ከማባባስ የሶማሊያን ህዝብ ያማከለ ሰላማዊ፣ ነፃ እና ተአማኒነት ያለው ያልተጓተተ ምርጫ ለማካሄድ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡