LatestNews

አየር መንገዱ በቫላንታይን ወቅት ብቻ 95 ሚሊየን የአበባ ዝንጣፊ ለተለያዩ ሀገራት ማጓጓዙን አስታወቀ

አየር መንገዱ 95 ሚሊየን የአበባ ዝንጣፊ ለተለያዩ ሀገራት ማጓጓዙን አስታወቀአዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 95 ሚሊየን የአበባ ዝንጣፊ ለተለያዩ ሀገራት ማጓጓዙን ገለፀ፡፡አየር መንገዱ 95 ሚሊየን የአበባ ግንጣይ ወይም ዝንጣፊውን ማጓጓዝ የቻለው በቫላንታይን ወቅት ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡የአየር መንገዱ ካርጎና ሎጀስቲክስ አገልግሎት እንዳታወቀው ከተጓጓዘው አበባ 1 ሺህ 600 ቶን ከናይሮቢ ሲሆን 3 ሺህ ቶን ደግሞ ከአዲስ አበባ ነው፡፡የአበባ ምርቱም ወደ ቤልጂየም፣ ኮትዲቯር፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ፣ አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓጉዟል፡፡