LatestNews

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የግማሸ ዓመት ብሔራዊ የሥራ ክንውን ምዘና እየመሩ ነው

የሚንስትሮች ምክር ቤት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በኮይሻ ማካሄድ ጀምሯል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማው ከአዲስ አበባ ውጭ ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።ለአንድ ቀን በሚቆይው የስራ ግምገማ ሁሉም የካቢኔ አባላት እየተሳተፉ ናቸው።እስካሁንም የኢኖቬሸንና ቴክኖሎጂ ሚኒቴስር፣ የፕላንና አቅድ ኮሚሽን፣ የውሃና ኤነርጂ ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ሚኒስቴር የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀማቸው ሪፖርቶቻቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ በእቅድ ዘመኑ ያሳኳቸውን ተግባራትና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በዝርዝር አቅርበዋል።ተጨማሪ ሳተላይት ወደ ህዋ ማምጠቅ፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ክለሳ ማድረጉን እና የታለንት ልማት ተቋም ማቋቋም መቻሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሪፖርቱ ጠቅሷል።የሐገሪቱን የ10 ዓመት መሪ አቅድ አዘጋጅቶ በሚኒስተሮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ተግባር መገባቱን ያቀረበው ፕላንና እቅድ ኮሚሽን በበኩሉ ኢትዮጵያ በ2030 ከአፍሪካ ሁለት ሀያላን ሀገራት አንዷ እንዲሁም ከዓለም 26 ሀያላን ሀገራት አንዷ ለማድረግ ያለመ በእቅድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በሪፖርቱ አንስቷል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባቀረበው እቅድ አፈፃጸም ሪፖርት የውሃ ተደራሽነትን በ40 ከተሞች ለማዳረስ አቅዶ በ6 ወራት ውስጥ የ8 ከተሞች ፕሮጀክት ተጠናቋል ብሏል። በዚህም 164 ሺህ ሰዎች ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ በሪፖርቱ ቀርቧል።የህዳሴ ግድብ አፈፃፀም 78 በመቶ ሲደርስ የኮይሻ ፕሮጀክት 42 በመቶ ላይ መድረሱንም ነው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኃይል ማመንጫ ግድቦች ዙሪያ በቀረበው ሪፖርት የጠቀሰው።የገቢዎች ሚኒስቴር በግማሽ ዓመት ዝርዝር እቅድ አፈፃፀምም ሪፖርት አቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።ሁሉም ተቋማት ባቀረቡት ሪፖርት ውይይት ከተደረገ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማጠቃላያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።