LatestNews

ዩናይትድ አየር መንግድ የቦይንግ 777 አውሮፕላንኖችን ከበረራ አገደ

ዩናይትድ አየር መንግድ በአሜሪካ አንድ አውሮፕላኑ ያጋጠመውን የሞተር ብልሽት ተከትሎ የቦይንግ 777 አውሮፕላንኖችን ከበረራ አገደ፡፡አየር መንገዱ በርካታ 777 ቦይንግ አውሮፕላኖችን በአለም አቀፍ ደረጃ ከበረራ ያገደው በአሜሪካ ዴንቨር ከተማ አንድ 777 አውሮፕላን የሞተር ብልሽት ካጋጠመው ብኋላ ነው፡፡የአሜሪካ የበረራ ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ ችግር የታየባቸው የቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ላይ አጠቃላይ ምርመራ እንዲጀመር ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡የጃፓን የበረራ ቁጥጥር መስሪያ ቤትም ተመሳሳይ ሞተሮች የተገጠመላቸውን የቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ወደ ሀገሪቱ የአየር ክልል እንዳይገቡ የሚያግድ መመሪያ አስተላለፏል፡፡የቦይንግ ኩባንያ እንዳመለከተው የጃፓን የበረራ ቁጥጥር ባልስልጣንና ሌሎች ያወጡትን የበረራ እገዳ በመደገፍም በአውሮፕላኖቹ ላይ ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs