የኮሚሽኑ የስራ አፈጻጸም
በ1 ሺህ 234 ወረዳዎች ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የመለየት ስራ መከናወኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ይሄንን ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የእስካሁን ተግባራትና ቀጣይ አቅጣጫ የሚገመግም መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በተካሄደበት ወቅት ሲሆን አካታችና አሳታፊ የሆነ የምክክር ተሳታፊዎች የመለየት ስራ የኢትዮጵያን 93 በመቶ የሸፈነ በ1 ሺህ 234 ወረዳዎች መካሄዱንም ጠቅሷል፡፡
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል ምክክሩን ለማድረግ የሚያስችል መድረክ በአዲስ አበባና በመቐለ ከተማ 22 ጊዜ ቢደረግም ባለው ምቹ ያልሆነ ሁኔታ በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች ምክክር ለማድረግ አለመቻሉን የጠቀሰው ኮሚሽኑ ዋናውን የምክክር ጉባኤ ማካሄድና ስምምነት የተደረሰባቸውን ውጤቶችና ምክረ ሀሳቦች ተፈፃሚነት ማመቻቸት ቀጣይ ስራዎቹ መሆናቸውንም ይፋ አድርጓል
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
