EthiopiaLatestNews

የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ለግማሽ ሚሊዮን ሰዎች

የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ለግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ከየካቲት 7 ቀን ጀምሮ ጀምሮ መሰጠት የጀመረውን 2ተኛውን ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ህብረተሰቡ ወደ አቅራቢያ ክትባት መስጫ ጣቢያዎች በመቅረብ እንዲከተብ ጥሪ ቀረበ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በመግለጫውም የሁለተኛው ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ እድሜያቸው 12 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉ በመንግስት ጤና ተቋማትና በጊዜያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያዎች ከትላንት ጀምሮ ማለትም ከየካቲት 7 እስከ የካቲት 16/2014 ዓ.ም መስጠት መጀመሩ ነው ቢሮው የጠቆመው።እስካሁን በአዲስ አበባ ከተማ በመጀመሪያ ዙር 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ሰዎች አንድ ጊዜ፤ 700 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ሁለት ጊዜ መከተባቸውን ቢሮው አስታውቆ በዚህ በሁለተኛው ዙር ዘመቻ ለግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ክትባት ለመስጠት መታቀዱን ጠቁሟል።ቢሮው አክሎም በአሁኑ ወቅት የቫይረሱ 4ኛ ዙር ማዕበል የተነሳበት በመሆኑ ህብረተሰቡ በመከተብና ሌሎችንም በማስከተብ ወረርሽኙን እንዲግታ ጠይቋል።

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision