EthiopiaNews

የውጭ ምንዛሬ

የገንዘብ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት 3.4 ቢሊየን ዶላር መድረሱን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይሄን ያስታወቀው ዛሬ ባወጣው የ18 ወራት ጥቅል ሪፖርቱ ላይ ነው።

ሚኒስቴሩ ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2025 አመት ባሉት ጊዜያት ውስጥ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በ240 በመቶ ማደጉን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ የወጪ ንግድ ገቢ ማደጉ ፣ የሃዋላ ገቢ መጨመሩ ፣ የውጭ እርዳታ እና ብድር እያደገ በመምጣቱ የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ጨምሯል ብሏል።

ሚኒስቴሩ በመደበኛው እና በትይዩ ገበያው መካከል ያለው የውጭ ምንዛሬ ልዩነት መጥበቡን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2024/25 በጀት ዓመት ከ6 ቢሊየን ዶላር በላይ ከሃዋላ አግኝታለች ብሏል።

መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ ነው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews