EthiopiaLatestNews

የዘመን ባንክ አክሲዮን ማህበር

የዘመን ባንክ አክሲዮን ማህበር በ2013 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።የባንኩ አጠቃላይ ሐብትም 52 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መድረሱንና ከ2012 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ36 ነጥብ 7 ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።ባንኩ ይህንን ባካሄደው 13ኛው መደበኛና 11ኛ ድንገተኛ የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ሲሆን የባንኩ የተከፈለ ካፒታሉም 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መድረሱንም ሰምተናል።ተቀማጭ የባንኩ ገንዘብም የ31 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ብልጫ በማሳየት በበጀት ዓመቱም 4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ገንዘብ መሰብስብ መቻሉንና ከወጭ ምንዛሪ ከማስገኘት አኳያም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ9 ነጥብ 3 በመቶ እድገት መመዝገቡ ተጠቅሷል።ከ13 ዓመታት በፊት በአንድ ቅርጫፍ የተመሰረተ የዘመን ባንክ አክሲዮን ማህበር አሁን ላይኔ 68 ቀርጫፎች ያሉት ሲሆን ለ1 ሺህ 151 ሰራተኞች የሥራ እድል መፍጠሩን ሰምተናል።ዘገባው የፍስሐ ደሳለኝ ነው።ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።Telegram: https://t.me/ebstvworldwideFollow us on: https://linktr.ee/ebstelevision#ኢቢኤስ#EBS