የድረ-ገጾች መጠለፍ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ድራይቭ ሰርጅ የተባለ የወንጀለኞች ቡድን በሺዎች የሚቆጠሩ ታማኝ ድረ ገጾችን በመጥለፍ ተጠቃሚዎችን ለአደገኛ የሳይበር ጥቃት እያጋለጠ መሆኑን አስጠነቀቀ።
ተቋሙ አጥቂዎቹ ክሊክ ፊክስ እና የሐሰት ማሻሻያ የተባሉ ረቀቅ ያሉ ስልቶችን በመጠቀም የዊንዶውስ እና የማክ ተጠቃሚዎችን የግልና የባንክ መረጃዎችን በመስረቅ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።
የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ በመለየት እና በመተንተን የሚታወቀዉ ሳይለንትፑሽ የተሰኘው ተቋምም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጋዊ ድረ-ገጾች መጠለፋቸዉን ተከትሎ ተጠቃሚዎች አደገኛ ለሆነ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸዉን ገልጿል።
በመሆኑም ከዚህ ለመዳን ማንኛውንም የብሮውዘር ማሻሻያ በመተግበሪያው ማስተካከያ ውስጥ ብቻ ማከናወንና ያልታወቁ የኮምፒውተር ኮዶችን ከመተግበር መቆጠብ ይገባል ሲል አሳስቧል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
