EthiopiaNews

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤቱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያሳዩት ጨዋነት ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስችሏል አለ

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በድህረ ምርጫ ወቅት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያሳዩት ጨዋነት ምርጫው ፍፁም ሰላም ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማስቻሉን ገልጿል፡፡

ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ላበረከቱት አወንታዊ አስተዋጽኦ ምስጋናውን ያቀረበው ምክር ቤቱ የምርጫ አሸናፊው ብልፅግና ፓርቲ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት አብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ጠቅሷል።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሕዝብን የሉዓላዊነት ስልጣን ያረጋገጠ መድረክ መሆኑን በጽኑ እንደሚያምን የጠቀሰው የጋራ ምክር ቤቱ አሸናፊ ለሆነው ለብልፅግና ፓርቲ እና በውድድሩ ተሳትፈው የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት ወንበሮች ላገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv