የ12ኛ ክፍል የሙከራ ፈተና
ለ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች የሙከራ ፈተና መሰጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስትር አስታውቋል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የዘንድሮውን የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በበይነ መረብ ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በመሆኑም ተማሪዎች የፈተና ሂደቱን ለመለማመድ በዴስክቶፕ ፣ በላፕቶፕ፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከዛሬ ግንቦት 07/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከፈተናው ቀን ድረስ መለማመድ እንደሚችሉም ተመልክቷል።
ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥርና የይለፍ ቃል በማስገባት የሙከራ ፈተናዎችን መፈተን እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤታቸው ማግኘት እንደሚችሉ የተገልጸ ሲሆን መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራሮችና ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ሂደቱን እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
