የ2026 ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የቁንጅና አሸናፊ
የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሩት ይርጋለም የ2026 ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የቁንጅና ውድድር አሸናፊ መሆኗን ይፋ አደረገ።
በ24ኛው የሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የቁንጅና ውድድር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ 50 ቆነጃጅቶች የተሳተፉ ሲሆን ራሳቸውን በመግለፅ ውድድር የተሻለ ውጤት ያሰመዘገቡ 25 ተወዳዳሪዎች ተለይተዋል።
በውድድሩ ሩት ይርጋለም የ2026 ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የቁንጅና ውድድር አሸናፊ በመሆን የክብር ዘውዱን መድፋት ችላለች ተብሏል።
የቁንጅና ውድድር አሸናፊዋ ሩት ይርጋለም በቀጣይ ኢትዮጵያን በመወከል በሚስ ወርልድ የአለም ቁንጅና ውድድር ላይ የምትሳተፍ ይሆናል።
ይሄው የቁጅና ውድድር በሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት ላለፉት 24 ዓመታት ሲካሄድ እንደነበር የገለፀው ሚኒስቴሩ ሞዴል ሀሴት ደረጀ ባለፈው አመት የውድድሩ አሸናፊ እንደነበረች አስታውሷል።
መረጃው ከባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
