EthiopiaNews

የ5 ሚሊዮን ኮደሮች መርሃ ግብር

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች መርሃ ግብር ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን ማጠናቀቃቸውን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን የኢትዮጵያ ኮደሮች መርሃ ግብር ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት መቻሉን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በተጀመረው “የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች” መርሃ ግብር ከ5 ሚሊየን በላይ ሰልጣኞች መመዝገባቸውን አስታውሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱን ገልፀው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በመርሃ ግብሩ የሚሰጠው ሥልጠና በነጻ የሚሰጥ እና የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው መሆኑ ይታወቃል።