InternationalNews

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ቢገልጹም ኢራን ይህንን የፕሬዝዳንቱን ንግግር አስተባብላለች።

ፕሬዝዳንቱ ሀገራቸው በኢራን ላይ ለሶስተኛ ተከታታይ ቀን ልታደርስ የነበረውን ጥቃት የሰረዘችው በመጨረሻው ሰዓት ላይ በተደረገ ከባድ ድርድር ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ በመደረሱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ትራምፕ በሁለቱ ሀገራት የተደረሰው የመጨረሻ ስምምነት የመግባቢያ ሰነድ በአውሮፓ በቀናት ዕድሜ ውስጥ እንደሚፈርም ቢገልጹም ኢራን ግን የፕሬዝዳንቱ ንግግር ያልተጨበጠ ነው ብላለች።

የኢራን ወጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኤስማኤል ባጌ በሰጡት ማብራሪያ በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተደረገ ባለው ድርድር አሁን ላይ ምንም ዓይነት የመጨረሻ ስምምነት ላይ አለመደረሱን ተናግረዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews