🗳️ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ውጤት
ክልሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 45 መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 35 መቀመጫዎች አሸንፏል።
እንዲሁም ኢዜማ 7 መቀመጫዎች፣ የጌዴኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት 1 መቀመጫና የወላይታ ዴሞክራሲያዊ ግንባር 1 መቀመጫ ሲያሸንፉ መስፍን ኢልታሞ የተባሉ የግል ተወዳዳሪ ደግሞ 1 መቀመጫ አሸንፈዋል።
በክልሉ ለምርጫ ከተመዘገቡ 2.8 ሚሊዮን ዜጎች መካከል 96 ከመቶው ድምጽ ሰጥተዋል።
