News

1 ቢሊዮን ዶላር ለአፍሪካ ፊልም ኢንዱስትሪ

አፍሪካ ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ የአፍሪካ የፊልም ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ አንድ ቢሊዮን ዶላር መድቢያለሁ ብሏል።

ከፈረንጆቹ 2024 ጀምሮ በአፍሪካ ላሉ የፊልም ኢንዱስቲሪዎች የስቱዱዮ ግንባታ ብሎም ለፊልም ቀረጻና ለፊልም ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል አንድ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን ነው ባንኩ ያስታወቀው።

የአፍሪኤግዚም በመባል የሚታወቀው ይኸው ባንክ የፈረንጆቹ 2024 ዓመት አየር ላይ ለሚውሉ የደቡብ አፍሪካ፣ ኬኒያና ናይጄሪያ ፊልሞች የገንዘብ ድጋፍ አድርጊያለሁም ብሏል።
አፍሪኤግዚም ባንክ በአህጉሪቱ ያሉ የጥበብ ስራዎች በመደገፍ የሚታወቅ ሲሆን ያሳለፍነው የፈረንጆቹ 2022 ለአፍሪካ የሙዚቃ፣ ፊልም፣ ስፖርትና ሌሎች ኪነጥበባዊ ክንውኖች የሚውል የ600 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።