EthiopiaNews

የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች

ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ 1 ሺህ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ልትገነባ ነው ተባለ ።

ለዚሁ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያም የዓለም ባንክ የ460 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ቀሪውን 63 ሚሊየን ዶላር ደግሞ በሌሎች ለጋሽ ተቋማት ይሸፈናል ተብሏል።

የ 523 ሚሊዮን ዶላር ዉጭ የተያዘለት ይህ ፕሮጀክት ከመፀዳጃ ቤት ግንባታ በተጨማሪ በ23 ከተሞች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎች ይከናወኑበታል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባትን የመቀሌ ከተማ የሚያካትት ሲሆን ኢትዮጵያም በከተማዋ የውሃ መሰረተ ልማቶችን ለማዳረስ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፓምፖች ለመግዛት 1 ሚሊየን ዶላር ወጪ ማድረጓም ተነግሯል ።
በፈረንጆቹ 2018 ግሎባል ዋተር ኢንተለጀንስ የተሰኘው ተቋም አደረኩት ባለው ጥናት በአገሪቱ ዘመናዊ መጸዳጃ የሚጠቀሙ የከተማ ነዋሪዎች 12 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ያመለክታል።