EthiopiaNews

ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ

የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኘ ለክልሉ መገናኛ ብዙኀን እንደተናገሩት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ለመቀበል ከሚደረግ ዝግጅት አኳያ ዩኒቨርሲቲው የሚጎድለው የለም ያሉ ሲሆን በክልሉ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው የቅድመ ምረቃና የድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አቅዶት ከነበረው ጊዜ መዘግየቱን ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ከክልሉ ሰላም ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ከጀመረ ጀምሮ ለድሕረ ምረቃ ተማሪዎች ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከአሁን በፊት ከነበሩት ከኮሮና ቫይረስና ከሰሜኑ ጦርነት መከሰት ጋር ተያይዞ ከፈጠሩ የመማር ማስተማር ችግሮች ትምህርት ወስደናል ያሉት ፕሬዝዳንቱ አሁንም ተማሪዎችን በምንቀበልበት ጊዜ የትምህርት ጥራቱን በማይጎዳ መልኩ ለማስኬድ ልምድና ዝግጅት አድርገናልም ብለዋል።