News

ሳፍሪኮም

የኬንያው ሳፋሪኮም ቴሌኮም ኩባንያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ስድስት ወራት 225 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

ተቋሙ ከሁለት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የትርፍ ጭማሪ ያሳየው በኢትዮጵያ ካደረገው ከፍተኛ የማስፋፊያ ስራ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ኤምፔሳን ጨምሮ በተፋጠነ የንግድ እንቅስቃሴ መጨመሩ ጋር ተያይዞ ኩባንያው ከ2 ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን የመዘገበ ሲሆን ደንበኞቹም16 ቢሊዮን ብር በላይ ማንቀሳቀሳቸውም አስታውቋል።