News

የኮታ ማሻሻያ

የዓለም የገንዘብ ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የአገሮች ኮታ ላይ ማስተካከያ ማድረጉ ተነገረ።

የኮታ ማሻሻያው እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራት ዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም ላይ የመወሰንና የመጠቀም አቅማቸውን ያዳብራል ተብሏል።
ድርጅቱ ባወጣው የዜና መግለጫ እንደሚለው የኮታ ጭማሪው አገሮች አሁን ባላቸው የአመራር ድርሻ የ50 ከመቶ ጭማሪን ያካተተ ሲሆን ይህም ደሃ ሀገራት ከተቋሙ ሀብት የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።