InternationalNews

የቻይና ብድር

ቻይና ለታዳጊ ሀገራት ያበደረችው ገንዘብ በትንሹ ከአንድ ነጥብ አንድ ትሪሊዮን ዶላር እንደሚበልጥ አንድ ጥናት አመለከተ ።
በአሜሪካው ኤይድ ዳታ በተባለ ሪፖርት እንደተጠቀሰው ይሄን ከፍተኛ መጠን ያለው ዶላር ከተበደሩት ታዳጊ ሀገራት 80 ከመቶ የሚሆኑት አሁን በከፋ የፋይናንስ እጥረት ውስጥ የሚዳክሩ ናቸው ብሏል።

ቻይና ከሰጠችው ብድር አብዛኛውም ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ለወጠኑት የቤልት ኤንድ ሮድ የመሰረተ ልማት ግንባታ የዋለ ነው ።
በታዳጊ ሀገራት ለመንገድ፣ ለአየር ማረፊያ፣ ለባቡር መስመርና ለወደብ ግንባታ የወጣው ይሄው ብድር በርካታ ታዳጊ ሀገራትና ቻይናን ወዳጅ ሲያደርግ ሀገሪቱንም የዓለማችን ከፍተኛዋ አበዳሪ አድርጓታል።