EthiopiaNews

የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ስርዓት

በኢትዮጵያ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት ላይ ተግባራዊ የተደረገውን የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ስርዓት ከመንግስት ተቋማት ይልቅ በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ቅቡልነቱ እያደገ መምጣቱን የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን አስታውቋል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አክሎም የዘንድሮውን የ2016 በጀት ዓመትን ጨምሮ ባለፉት 2 ዓመታት ከ38 ሺህ በላይ የሚሆነው የንግዱ ማህበረሰብ መንግስት በሚያወጣቸው የኤሌክትሮኒክስ የንብረት ግዥ ጫረታ ላይ በንቃት ተሳትፏል ብሏል።