EthiopiaNews

ውድመት በአፍሪካ

በፈረንጆቹ 2022 ኢትዮጵያን ጨምሮ 110 ሚሊዮን አፍሪካዊያን ግምቱ 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የኢኮኖሚ ውድመት ገጥሟቸዋል ተባለ።

ቻይና ዴይሊ የጠቀሰው የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ሪፖርት ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ጉዳቱ የገጠማቸው በተለይ በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት ነው ብሏል። በዚሁ ጊዜ 5 ሺህ አፍሪካዊያን በረሃብ የሞቱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 48 ከመቶ የሚሆኑት በድርቅ፣ ሌሎች 43 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ጎርፍ ሕይወታቸውን አጥተዋል።