EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንን አርማ እና ስያሜ በመጠቀም ከጉምሩክ የተወረሱ ዕቃዎችን በቅናሽ እናቀርባለን በማለት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሀሰተኛ ምስሎችን በመጠቀም በርካታ ግለሰቦች እየተጭበረበሩ መሆኑን ኮሚሽኑ አመልክቷል።

በመሆኑም ህብረተሰብ ከእነዚህ አጭበርባሪዎች ራሱን እንዲጠብቅ ያሳሰበው ኮሚሽኑ  በኮንትሮባንድ የተወረሱና በሽያጭ የሚተላለፉ ዕቃዎች የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በኮሚሽኑ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እና ተዓማኒነት ባላቸው በተለያዩ የኮሙኒኬሽን አማራጮች የሚተላለፉ መሆኑንም አሳውቋል።

ህብረተሰቡ መሰል መረጃዎችን ሲመለከት እውነትኛነታቸውን እንዲረጋግጥና ሀሰተኛ ሆነው ሲያገኝ ጥቆማ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡