የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ባወጣው መግለጫ በሰኔ 2018 አ.ም የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ከባለፈው 2017 ዓ. ም ከነበረው የ13.9 በመቶ የዋጋ ግሽበት ጋር ተመሳሳይ ነው ብሏል።
የምግብ እና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ በ15 ነጥብ 1 በመቶ የጨመረ ሲሆን በዋናነት አትክልት ፣ ስጋ ፣ የወተት ተዋፅኦዎች ፣ እንቁላል ፣ ፍራፍሬ እና የመሳሰሉት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በመጨመራቸው የተመዘገበ ጭማሪ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 12 ነጥብ 2 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት 14 ነጥብ 3 በመቶ ፣ ኮሚኒኬሽን 8 ነጥብ 9 በመቶ ፣ምግብ ቤቶች እና ሆቴሎች 12 በመቶ እና ሌሎች እቃዎች እና አገልግሎቶች 17 ነጥብ 9 በመቶ ሆነው ተመዝግበዋል።መረጃው ከኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የተገኘ ነው።
