EthiopiaNews

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት መምሪያ በውጭ የሚኖሩ እና ከአካባቢው ርቀው የሚገኙ ባለይዞታዎች ከዚህ ቀደም የተቀመጠው ቀነ ገደብ እንዲራዘምላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት እስከ ሐምሌ 30 2018 ዓ.ም መራዘሙን ገልጿል።

በተራዘመው የጊዜ ገደብ ውስጥ ባለይዞታዎች የስም ዝውውር፣ የሊዝ ዘመን ያጠናቀቁ እና የሊዝ ጊዜ የተራዘመላቸው ጉዳዮች፣የዞኒንግ ለውጥ፣የጨረታ መሬት ውዝፍ ክፍያዎች፣ሌሎች ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ክፍያዎች እና የዲጂታል መሬት ይዞታ መረጃ ቅድመ ክፍያዎችን በተወሰነው ጊዜ ውስጥ እንዲያጠናቅቁ መመሪያው አሳስቧል።

በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያዎችን በማይፈጽሙ አካላት ላይ በአዲሱ ታሪፍ መሠረት የሚከፈል መሆኑን መምሪያው አሳውቋል።

በተመሳሳይም ውዝፍ ግብር ያልተከፈለባቸውን በጨረታ የተላለፉ መሬቶች ወደ መሬት ባንክ የሚገቡ መሆኑን ገልጾ ግብር ከፋዩ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግብሩን እንዲከፍል መምሪያው አሳስቧል።መረጃው ከሃዋሳ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።