EthiopiaNews

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይሄን ያሉት የተቋማቸውን የ2018 በጀት አመት አፈፃፀም በተመለከተ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ያገኘው ገቢ የእቅዱን 99 ነጥብ 7 በመቶ ያሳካ ነው ብለዋል።

ፍሬህይወት ታምሩ ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት ካስገባው 162 ቢሊየን ብር አንፃር ሲታይ የ2018 ገቢው በ32 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በተገባደደው 2018 በጀት አመት ካስገባው ገቢ ውስጥ 31 ነጥብ 1 ከመቶ ከኢንተርኔት እና ዳታ አገልግሎት የተገኘ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል።