ባለስልጣን መ/ቤቱ ይሄን ያለው በተቋማቱ ላይ የወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ባደረገው ምዘና ክፍተት በተገኘባቸው 9 የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት ላይ እንደ ጥፋት ደረጃቸው ከፈቃድ ስረዛ እስከ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሚደርስ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።
ባለስልጣኑ ባካሄደው ዝርዝር ምዘና መሰረት ፦2 የምርመራ ተቋማት ፈቃዳቸው መሰረዙን ፣ 3 ተቋማት ለሦስት ወር መታገዳቸውን ፤2 ተቋማት ለአንድ ወር መታገዳቸውን እና 2 ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልጿል፡፡
ይሁን እንጂ ባለስልጣን መ/ቤቱ የተቋማቱን ዝርዝር ከመግለፅ ተቆጥቧል። መረጃው ከአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የተገኘ ነው።
