በበሽታው እስካሁን 3200 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ባለፉት 10 ቀናት ብቻ አንድ ሺህ ያህል ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
ይህ የተገለፀውም በዲሞክራቲክ ኮንጐ ለ17ኛ ጊዜ የተቀሰቀሰውን ወረርሽኝ አስመልክቶ ትላንት እሁድ በወጣ ሪፖርት ነው።
በፈረንጆቹ ግንቦት አጋማሽ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ዓይነት ቡንዲቡጋዮ በተባለ የቫይረስ ዓይነት የሚከሰት ሲሆን ይሄ የኢቦላ ዝርያ ምንም ዓይነት እውቅና ያለው ክትባትም ሆነ መድሃኒት የለውም።
የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ከበሽታው ታማሚዎች 90 ከመቶ የሚሆኑት ኡጋንዳና ደቡብ ሱዳንን ከምታዋስነው ኡቱሪ ግዛት የተመዘገቡ ናቸው።
