በማእከላቱ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት ርዕሰ ብሔር ታዬ አፅቀስላሴ የቻይና-አፍሪካ ሆስፒታሎች ህብረት የኢንዶስኮፒክ እና የሚኒማል ኢንቬሲቭ ቀዶ-ህክምና የትብብር ፕሮግራምን ትናንት በይፋ አስጀምረዋል።
ርዕሰ ብሔሩ የቻይና-አፍሪካ ሆስፒታሎች ህብረት የትብብር ፕሮግራም በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን አጋርነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
የማሰልጠኛ ማዕከላቱ ለቀጣዩ ትውልድ የኢትዮጵያ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ማፍሪያ ሆነው ያገለግላሉ ያሉት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ፣ እነዚህ ማዕከላት ለመላው የአፍሪካ አህጉር የእውቀት እና የላቀ አገልግሎት ማዕከል እንደሚሆኑም ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ በቻይና እና በአፍሪካ መካከል ያለው ትብብር በሁሉም ዘርፎች እያደገ መሆኑን ተናግረዋል።
የረቀቀ የቀዶ ህክምና ማሰልጠኛ ተቋሞቹ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ሊቢያ፣ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ከ30 በላይ ተሳታፊዎች በመጀመሪያ ዙር ስልጠና መስጠት ጀምረዋል።
በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን ተቋማዊ ትብብር የሚያጠናክር የመግባቢያ ስምምነትም ተፈርሟል።መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
