የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን 54 የሚዲያ ተቋማት እና 461 ጋዜጠኞች የምክክሩን ሂደት እየዘገቡ መሆኑን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ይሄን ያለው የሚዲያ ተቋማትን የዘገባ ተሳትፎ እና የመረጃ ተደራሽነትን በተመለከተ ባዘጋጀው ሪፖርት ላይ ነው።
ኮሚሽኑ ሀገራዊ ምክክሩ ከመካሄዱ በፊት በርከት ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫና የአጋርነት ማጠናከሪያ መድረኮችን ከመገናኛ ብዙሃን ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር መካሄዱን አስታውሷል፡፡
በእነዚህ መድረኮች በተፈጠረው ግንዛቤና በተደረሰው መግባባት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት በርካታ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች እንዲሳተፉ መደላድል ከመፍጠሩ ባሻገር መረጃዎች በሙያዊና ሀገራዊ ሃላፊነት እንዲሰራጩ ማስቻሉን በዚሁ ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡
ተሳትፎው ሁሉንም የመገናኛ ብዙሃን አይነቶች እንዳካተተ እንዲሁም የተቋማቱን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ባከበረ መልኩ መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርጉበት ነፃነት በኮሚሽኑ በኩል የተረጋገጠ መሆኑንም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡
ኮሚሽኑ በምክክሩ ቦታ ተገኝተው እንዲሁም ከኮሚሽኑ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች እና በስፍራው ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን እየተጋሩ ለህዝብ እያደረሱ ላሉ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርቧል፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን ተሳትፎ እስከ ድህረ ምክክር አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቋል፡፡
ህብረተሰቡ ወደ ምክክሩ ቦታ እየገቡ መረጃዎችን ተደራሽ ከሚያደርጉ መገናኛ ብዙሃንና ባለሙያዎች መረጃዎችን በማግኘት ከተዛቡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡መረጃው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
