InternationalNews

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቱርክ እያሉ በደህንነት ስጋት ምክንያት ወደ አገራቸው ለመመለስ አውሮፕላን መቀየራቸውን አረጋግጠዋል።

ባለፈው ሐምሌ መጀመሪያ ለኔቶ ጉባኤ ቱርክ የነበሩት ትራምፕ ከኢራን ሊቃጣ የነበረ ጥቃትን በመስጋት ከኤየር ፎርስ ዋን አውሮፕላን በድብቅ ወርደውና በምግብ ማመላለሻ መኪና ወደሌላ አውሮፕላን ገብተው መብረራቸውን አምነዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ በወቅቱ የደህንነት ሰራተኞች አውሮፕላን እንዲቀይሩ እንዳዘዟቸውና ከእነሱ ትዕዛዝ ውጪ መሆን ስለማይችሉ ትዕዛዙን አክብረው አነስተኛ አውሮፕላን ቀይረው መብረራቸውን ተናግረዋል፡፡

በኤየር ፎርስ ዋን ላይ የነበሩትን ሌሎች ሰዎች ለአደጋ አጋልጠዋል ተብለው የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ ኢራን ጥቃት ብትፈጽም እንደውም ከፕሬዝዳንታዊ አውሮፕላኑ ይልቅ እኔ በነበርኩበት ወታደራዊ አውሮፕላን ላይ ያለው ስጋት ይበልጥ ነበር ብለዋል፡፡