EthiopiaNews

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በ2019 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 13 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን ተናገሩ።

ሚነስትሩ ይሄን ያሉት ከወጪ ምርት ላኪዎች ጋር በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ባካሄዱት ውይይት ነው።

ሚኒስትሩ በ2019 በጀት ዓመት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ይበልጥ ለማሳደግ የ13 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ግብ የተቀመጠ መሆኑን ገልፀው ይህንን ለማሳካትም በሥራ ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

እቅዱን እዉን ለማድረግም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ላኪዎችን በመደገፍና አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ለ2019 በጀት ዓመት ስኬታማነት ምርቶችን በብዛት ከመላክ ባለፈ እሴት በመጨመርና ጥራትን በማረጋገጥ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባ እና አዳዲስ ዓለም አቀፍ የገበያ መዳረሻዎችን መፈለግ እንደሚያሻ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከጠቅላላ የወጪ ንግድ ከ11 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ይታወሳል።መረጃው ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።