EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2018 በጀት ዓመት 36.08 ቢሊየን ብር ግብር መክፈሉን አስታወቀ።

ባንኩ ይሄን ያለው በታማኝነት እና በኃላፊነት የግብር ከፋይነቱን በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝ ባወጣው አጭር መግለጫ ነው።

ባንኩ በ2018 በጀት ዓመት 80 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱ የሚታወስ ነው።

ባንኩ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 707 ነጥብ 47 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ በመሰብሰብ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘቡን ከ2 ነጥብ 4 ትሪሊየን ብር በላይ ማድረሱ ይታወሳል።መረጃው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው።